Sunday, November 22, 2020

ጥንታዊ የጎንደር ሰፈር ስሞች

ጥንታዊ የጎንደር ሰፈሮች ስሞች 

1. *ጥንታዊ ናቸው የሚባሉ እና ተመዝግበው የሚታወቁ
1.1. አደናግር፡-
ይህ ስም ከፋሲል ግንብ 12 በሮች ውስጥ አንደኛው
የሚጠራበት ነው፡፡ በሩ በምስራቁ የግቢው ገጽ አዛዥ ጥቁሬ
እና ቀስተደመና በር በሚባሉ ሌሎች የግቢው በሮች
በመካከል የሚገኝ ነው፡፡ አደናግር ተብሎ የሚታወቀው
ሰፈርም የሚገኘው ከበሩ ግንባር ነው/ ነበር፡፡ አደናግር
ለምን ለአካባቢው መጠሪያ ሊሆን እንደቻለ በብዙዎች
የሚነገር አፈ ታሪክ የሰፈሩ ስም ከገቢው በር ስያሜ
እንደተወሰደ ያረጋግጣል፡፡ የሰፈሩ ስፋት በምስረቅ እስከ
አርባዕቱ እንስሳ፣ በሰሜን እስከ ደብረ ብርሀን ስላሴ፣
በደቡብ እስከ ግራ ደንበር ይደርስ እንደነበር ይነገራል፡፡
ግንቡ በሮች የተሰሩትም ሆነ የተሰየሙት በአጼ ፋሲል ዘመን
በመሆኑ ሰፈሩም ስያሜውን ያገኘው ከዚያ ዘመን ጀምሮ
ሊሆን ይችላል፡፡
(በዚህ በር ነገስታቱንና እቴጌዎችን ከአይንና ከጥቃት
ለመከላከል፤ እንደ ነጉሶችና ነግስቶች ለብሰውና መስለው
ከንጉሶችና ንግስቶች ጋር የሚወጡና የሚገቡ ሰዎች ነበሩ፡፡
እነኝህ ሰዎች አሳሳቾች ወይም አደናጋሪዎች በመባል
ይታወቁ ነበር፡፡ በሩም ስያሜንውን ያገኘው በእነዚህ ሰዎች
እንደሆነ ይነገራል፡፡ የበሩ እንዳለ ሆኖ ሰፈሩም አደናጋሪዎች
በብዛት ሰፍረውበት ስለነበር ነው ይባላል፡፡)
1.2. እርግብ በር፡-
ይህ ስ ከ12ቱ የግቢው ስሞች አንደኛው ነው፡፡ ከበሩ ፊት
ለፊት ያለው ሰፈር እርግብ በር በመባል ይታወቃል፡፡ አጼ
ፋሲል እርግብ ያረቡ እንደነበርና ያረቡበት የነበረ ሰፈር ከዚሁ
በመሆኑ በዚህ ምክኛት ርግብ በር ተብሎ ተጠራ፡፡ የእርግብ
በር ሰፈር የአባ ጃሌ ተክለ ሀይማኖት ቤተ ክርስትያን አካባቢ
ጀምሮ እስከ እስከ ፒያሳ ይሸፍን እንደነበር ይገመታል፡፡
አርግብ የማርባት ልምድ ያላቸው አጼ ፋሲል ብቻ
በመሆናቸው የሰፈሩ ስያሜ በእርሳቸው የንግስና ዘመን ሊሆን
ይችላል፡፡ በአሁኑ ሰዐት ግን ሰፈሩ እርግ በር በሚል እነደ
ጥንቱ እምብዘም አይታወቅም፡፡
1.3. እንኮየ መስክ፡-
እስከ አሁን ድረስ በከተማው ውስጥ በቀደምት ስማቸው
ይታዎቃሉ ከሚባሉት ሰፈሮች እንኮየ መስክ አንደኛው ነው፡፡
ይሁኑ እንጅ መጀመሪያ በስሙ ይጠራ የነበረው አካባቢ ሁሉ
በስሙ እየተጠራ አይደለም፡፡ የእንኮየ መስክ ሰፈር
የሚገኘው ከፋሲል ግንብ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በቀኝ
ቤትና በእጨጌ ሰፈሮች መካከል ይገኘል፡፡
ሰፈሩ ለምን እንኮየ መስክ ሊባል እንደ ቻለ የተለያዩ አፈ
ታሪኮች ይነገራሉ፡፡ በብዙዎች የሚነገረው ግን ወይዘሮ
እንኮየ ሰፍረውበት ስለነበረ በወይዘሮዋ ስም እንደተጠራ
ይታሰባል፡፡ ወይዘሮ እንኮየ የአጼ በካፋ ሚስት፣ የእቴየ
ምንትዋብ እናት ነበሩ፡፡ የሰፈሩ ስም አመጣጥ ከወይዘሮ
እንኮየ አሰፋፈር ጋር ከተገናኘ ሰፈሩ በስሙ መጠራት
የጀመረበት ጊዜም ከአጼ በካፋ ወይም ከቋረኛ ኢያሱ ጊዜ
ጀምሮ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህኛው አፈ ታሪክ ሌላ
ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ይኸውም እንከየ መስክ በሚገኝበት አካባቢ
እንኮየ በር የሚባል የግንቡ በር አለ፡፡ ስለዚህ በሩ እንዴት
እንኮየ በር ተብሎ ሊጠራ ቻለ ነው፡፡ ምንአልባትም በአጼ
ፋሲል ዘመን በሌላ ስም ሲጠራ ቆይቶ በእንኮየ ስም ዘግይቶ
በአጼ በካፋ ወይም በኢያሱ ዘመን ተቀይሮ ሊሆን ይችላል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ስያሜው ከአጼ ፋሲል ጀምሮ የነበረ
ነው የሚሉ አሉ፡፡ ለዚህም እንኮየ የምትባል ከአጼ ፋሲል
ገረዶች መካከል ሃላፊ ሆና ትኖርበት ስለ ነበር ወይንም
እንኮየ የምትባለው የንጉሱ ቅምጥ ትኖርበት ስለነበር ነው
የሚሉ አሉ፡፡
1.4. ፋሲለደስ፡-
ፋሲለደስ ይባል የነበረው ሰፈር ስሙን የወሰደው አጼ ፋሲል
በአሰሩትና ፋሲል መዋኛ ገንዳ ግቢ ውስጥ ይገኝ ከነበረ
ቅዱስ ፋሲለደስ ቤተ ክርስቲያን ነበር፡፡ የፋሲለደስ ሰፈርና
የቤተ ክርስቲያኑ በሰሜን እስከ ቀሃ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያነ
ሰበካ፣ በምዕራብና በደቡብ እስከ መጥምቁ ዮሀንስ ሰበካና
በምስራቅ እስከ ሀይሌ ሜዳ ይባል የነበረውን ይሸፍን ነበር፡፡
በስሙ ይጠራበት የነበረውን ሁሉንም ባይሸፍንም
በመዋኛው ገንዳ አካባቢ ፈጽሞ አልጠፋም፡፡
1.5. ዋላጅ፡-
በጎንደር ከተማ ስር ነበሩ ተብለው በቄስ ገሪማ ታፈረ (የፕ/
ረ ኃይሌ ገሪማ አባት) ከተመዘገቡት ሰፈሮች አንዱ ዋላጅ
ሲሆን ሰፈሩ አሁንም በዘሁ ስም ነው የሚጠራ ነው፡፡ ነገር
ግን ዋልጅ የሚለው ሰፈር የጎንደር ከተማ ከመቆርቆሩ
በፊትም እነደ ነበር ይነገራል፡፡ ከጎንደር ከተማ መቆርቆር
በፊት እንደነበረ ቢታሰብም መቼ ጀምሮ ዋላጅ ተብሎ
መጠራት እንደጀመረና የቃሉ ትርጉም በትክክል አይታዎቅም፡፡
እንደአንዳንድ አባቶች ከሆነ ዋላጅ የሚለው ቃል ለአካባቢው
መታወቂያ ሊሆን የቻለው በአጼ ናኦድ
ዘመን /1487-1500/ ስድስት የተወለዱ ስድስት የተወደዱ
ተብለዎ ለሚታወቁ ሰዎች ርስት ጉልት ሆኖ ተሰጣቸው፡፡
ተወላጅ- ስድስቱ የተወለዱ ከንቲባ ተስፋ የሚባል የቤተ
መንግስት ባለሟል ልጆች ነበሩ፡፡ አገሩ ሊሰጣቸው የቻለው
የተወለዱት በቤተ መነግስት ተወላጅነታቸው የተወደዱት
አባታቸው ታማኝ፣ የታፈረና የተከበረ የቤተ መንግስቱ
አገልጋይ ስለነበረለአባታቸው መልካም ስራ ውለታ ነበር፡፡
ስድስቱ የተወለዱት በቤተ መንግስት ተወላጅነታቸው
ከነበራቸው ክብር ጋር ባለርስት ጉቶች ስለነበሩ ከይዞታቸው
በኋላ አገሩ የውላጅ አገር ተብሎ ተጠራ፡፡ጊዜ እየረዘመ
ሲሄድ ግን አገሩ የውላጅ መባሉ ቀርቶ ውላጅ በኋላም ዋላጅ
ወደሚል ቅላጼ ተቀየረ፡፡
ዋላጅ ከአካባቢው የመጀመሪያ ሰፋሪዎች አባት ስም ነው
የሚሉም አሉ፡፡ ዋላጅ ከርከር የሚባል ወንድም ነበረው፡፡
የከርከር ልጆች የሰፈሩበት አገርም ከርከር ተብሎ ስለተጠራ
የሁለቱ ወንድማማቾችና ዘሮቻቸው አገር ከርከርና ዋላጅ
ተብሎ እንደተጠራ፤ በአሁኑ ወቅት ግን ከርከርና ዋላጅ
የሚባሉት አካባቢዎች መጠሪያዎቻቸው ተለያይተው የሚታቁ
የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ናቸው፡፡
ከአካባቢው አባተች ዋለጅ ከ44ቱ ጎንደር ውስጥ እንደነበር
የሚተርኩ አሉ፡፡ እንዲያውም 44ቱ ጎንደር የሚለው መጠሪያ
ሊወጣ የቻለው ከ44ቱ ቤተክርስቲያኖች ስለ ነበር፤ ከ44ቱ
ውስጥ ደግሞ 4ቱ የሚገኙት በዋላጅ ነበር፡፡ ቤተ
ክርስቲያኖቹም ቅዱስ አማኑኤል፣ ድባ ሀዋርያት /ድርቡሾች
አቃጥለውት ኖሮ በ1951 ቤተ ክርሰቲያኑ ተሰርቶ የአቦ
ታቦት ስለገባ ድባ አቦ እየተባለ ይታወቃል/፣ ምንጭርና
ጊወርጊስና ቸሆን ማርያም ይባሉ እንደነር ይነገራል፡፡
በዋላጅ በአሁኑ ወቅት *ሸንበቂት የምትባል ከተማ
ተመስርታበታለች፡፡ ሸምበቂት የሚለው መጠሪያ አሁን
ከተማዋ ከምትገኝበት ምዕራብ አቅጣጫ ብዙ ኪሎ
ሜትሮች ራቅ ብሎ በሸንበቆ ተሸፍኖ ይገኝ ከነበረና
ሸንበቆች ተብሎ ከሚጠራው ዳገታማ አካባቢ የተወሰደ ነው
ይባላል፡፡ ሸንበቂት ከጎንደር ከተማ ወደ ደባርቅ በሚወስደው
አውራ መንገድ ዳር ከከተማው ከ9/10 ኪሎ ሜትሮች ርቀት
ላይ ትገኛለች፡፡
(*አሁን ከተማዋ ሸምበቂት ከመባሏ በፊት ፈላሻ ሜዳ
በመባል ትታወቅ ነበር፡፡ ፈላሻ ሜዳ የተባለው ፈላሻዎች
በብዛት ሰፍረውበት ስለነበር ነው፡፡ ፈላሻዎች ለባለርስትና
ጉልት ሸክላ ብረትና ልብስ በመስራት ያገለግሉ ነበር፡፡
ከፈላሾች ጋር ቅማንቶችም ያገለግሉ እንደነበር ይነገራል፡፡)
1.6. አዘዞ፡-
*አዘዞ የሚለው መጠሪያ የጎንደር ከተማ ከመመስረቱ
በፊትም እንደነበር የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ (*ስርግው፣
አማርኛ የቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት፣ ገጽ 90፤)፡፡ አዘዞ
ለሚለው ቃል አመጣጥ ከአጼ ሲስንዮስ የመጨረሻና ከአጼ
ፋሲል የመጀመሪያ አመታት ጋር አገናኝተው የሚተርኩ አሉ፡፡
ከነዚህም መካከል አንደኛው **አጼ ሲስንዮስ /ከ1598/9 –
1624/ አባቶቻቸው ይከተሉት የነበረውን የኦርቶዶክስ
እምነት ትተው የካቶሊክ እምነት ተከታይ ሆኑ፡፡ በካቶሊክ
እምነት ከመጠመቃቸው በፊት ግን በኋላ አዘዞ ተብሎ
በሚጠራው አካባቢ የኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን አስተክለው
ስለነበር ሀይማኖታቸውን ከለወጡ በኋላ የካቶሊክ ስርዓተ
ቅዳሴና ጥምቀት እንዲካሄድበት አደረጉ፡፡ ህዝቡም ነባሩን
እምነት ትቶ በአዲሱ እንዲጠመቅ አወጁ፡፡ ይሁንጅ ካህናቱና
ህዝቡ አዲሱን ሀይማኖት አንቀበልም በማለታቸው በተነሳው
ጦርነት ብዙ ህዝብ አለቀ፡፡ ብዙ ካህናትና መነኮሳትም
ሀይማኖታቸውን በለወጡት እጅ ተገድለው መስዋትነትን
ለመቀበል ንጉሱ ወደሚገኙበት እየመጡና ንጉሱንም
እያወገዙተገደሉ፡፡ አጼ ሲስንዮስ አዲሱን ሀይማኖት ህዝቡ
እንዳልተቀበላቸው ሲያውቁ ዙፋናቸውን ለልጃቸው
አስረከቡ፡፡ የሮም ሀይማት ትርከስ፤ የእስክንድር ሀይማት
ትመለስ፤ ሲስንዮስ ይፍለስ፤ ፋሲል ይንገስ የሚል አዋጅ
ተነገረ፡፡ አጼ ፋሲልም ከነገሱ በኋላ ከሸዋ የአቡነ ተክለ
ሀይማኖትን ታቦት አስመጥተው በመስቀል ባርከው
በወንጌል ሰብከው ብዙዎች ሰማዕትነት በወደቁበት አካባቢ
ያስተክሉት ብለው አእጨጌ በትረ ጊወርጊስን ስለ አዘዙ፤
አዘዙ ከሚለው ቃል አዘዞ የሚል ቃል ወጥቶታል የሚል
ነው፡፡
በሌላ በኩል ዶክተር ስርግው ሀብተ ስላሴ እንደጻፉት ከሆነ
ንጉሰ ነገስቱ /አጼ ሲስንዮስ/ ደምቢያ ውስጥ ካሉት ሀገሮች
መልካሙን ምድር አዘዞን መረጠ፡፡ … በቦታውም መልካምነት
የአዘዞ ተክለ ሀይማኖትን ቤተ ክርስቲያን መስራት ጀመረ፡፡

Saturday, November 21, 2020

ጎንደር 44ቱ ታቦት

1 አዘዞ ተ/ሃይማኖት 



2 ፊት አቦ



3 ፊት ሚካኤል

4 አደባባይ ኢየሱስ

5 ግምጃ ቤት ማርያም

6 እልፍኝ ጊዮርጊስ

7 መ/መ/መድኃኔዓለም


8. አቡን ቤት ቅ/ገብርኤል




9 አባ እንጦንሰ 


10 ፋሲልደስ

11 ጠዳ እግዚአብሔር

12 አርባዕቱ እንስሳ

13 ቀሐ ኢየሱስ



14 አበራ ጊዮርጊስ


15 አደባባይ ተክለሃይማኖት

16 ደብረ ብርሃን ሥላሴ



17 ዳረገንዳ ኤዎስጣቴዎስ

18 አጣጣሚ ሚካኤል


19 ጐንደር ሩፋኤል

20 ደፈጫ ኪዳነ ምህረት

21 ቅ.ዮሐንስ መጥምቅ



22 ጐንደር ልደታ ማርያም

23 ሠለስቱ ምዕት


24 ጎንደር በአታ ለማርያም

25 ወ/ነጐድጓድ ዮሐንስ




26 ጐንደር ቂርቆስ

27 ጐንደር ሐዋርያት(ጴጥሮስ ወጳውሎስ )

28 ፈንጠር ልደታ

29 ሰሖር ማርያም

30 ወራንገብ ጊዮርጊስ

31 ምንዝሮ ተ/ሃይማኖት

32 ደ/ፀሐይ ቊስቋም

33 ደ/ምጥማቅ ማርያም

34 አባ ሳሙኤል



35 ጐንደሮች ማርያም

36 ጐንደሮች ጊዮርጊስ

37 አባ ጃሌ ተ/ሃይማኖት


38 ዐቢየ እግዚእ.ኪ/ምህረት


39 ብላጅግ ሚካኤል

40 አሮጌ ልደታ

41 ጫጭቁና ማርያም

42 ጋና ዮሐንስ

43 አይራ ሚካኤል

44 ዳሞት ጊዮርጊስ

Friday, July 13, 2018

ጎንደር እንዴት ተመሰረተች

ጎንደር እንዴት ተመሰረተች?
1623 ሰኔ ወር ላይ አፄ ሱንስዮስ ለልጃቸው ለአፄ ፋሲል በህይወት እያሉ ስልጣናቸውንያስተላልፋሉ፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ሜንዴዝ የሚባል የካቶሊክ ሚሽነሪ መጥቶ ነበር፡፡ አዘዞ (አሁን አፄ ቴዎድሮስ ኤርፖርት ያለበት ቦታ) ጎርጎራ እና ደንቀዝ የሚባሉ ቦታዎች ሶስት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያኖች ተሰርተው ነበር፡፡ ደንቀዝ ላይ ያለው እንደ ቤተመንግስትም ያገለግል ነበር፡፡ አፄ ሱስንዮስ ስልጣናቸውን አስተላልፈው ያረፉትም በዚሁ የካቶሊክ ደብር ውስጥ ሆነው ነው፡፡ ከዚያ በኋላ አፄ ፋሲለደስ የህዝቡን ፍቃድ ለማሟላት ኢየሱሳውያኑን ከሃገር አባረሩ፡፡ ስልጣናቸውን ተቀብለው አፄ ከተባሉ 4 ዓመታት በኋላ አሁንቤተመንግስታቸው ከሚገኝበት ቦታ መጥተው የዛሬዋን ጎንደር ሊመሰርቱ ችለዋል፡፡
ለምን ወደ ጎንደር መምጣት አስፈለጋቸው
እዚያው አባታቸው የነበሩበት ቦታ ላይ መንግስታቸውን መመስረት አይችሉም ነበር? በሶስት ምክንያቶች ነው እንደዚያ ያደረጉት። አንደኛው ከእምነት አንፃር፣ ጎርጎራ ካቶሊካውያኑ የነበሩበት ቦታ ስለነበር የረከሰ ነው ተብሎ ታመነ። ስለዚህ አዲስ ቦታ መቀየር አስፈለጋቸው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት፣ ጎርጎራ ወባማ አካባቢ ስለነበር ሰራዊታቸውን ፈጀባቸው፡፡ እናም ከጤና አኳያ የአሁኑ ጎንደር ተመራጭ ሆነ፡፡ ሦስተኛው ምክንያት፣ ጎንደር ወይና ደጋ አየር ንብረትና 40 በላይ ምንጮች ያላት ነበረች፡፡ በወንዞችም የተከበበች በመሆኗም የሰራዊቱን የውሃ ፍላጎት ታሟላ ነበር፡፡
      አሁን ቤተ መንግስቱ ያለበት ቦታ 2200 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ አለው፡፡ ዙሪያውን ደግሞ እስከ 3 ሺህ ሜትር ከፍታ ያላቸው ተራራዎች አሉ። እነዚህ ተራራዎች የአየር ወለድ በሽታ ቢመጣ ወደ ከተማዋ አያስገቡም/ አያሳልፉም ተብሎ ይታሰባል፡፡ ከጦር ስትራቴጂ አንፃርም በተራራ መከበቧ ጠላት በቀላሉ እንዳይገባ ይከላከላል፡፡ ተራራዎቹ በትልልቅ ዛፎች የተጠቀጠቁ መሆናቸውም የማገዶ ፍጆታን ያሟላሉ፡፡ በእነዚህና በሌሎች ምክንቶች ጎንደር 1628 . ተመሰረተች፡፡
        አፄ ፋሲለደስ 1660 . ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ፣ የጎንደር ህዝብ ብዛት 27 ሺህ ደርሶ ነበር። ይሄ የሚያሳየው ከተማዋ በወቅቱ እጅግ ሰፊ መሆኗን ነው፡፡ በእነ እቴጌ ምን ትዋብ ዘመን ደግሞ የህዝብ ብዛቱ እስከ 100 ሺህ ደርሶ ነበር፡፡ ከብሄር፣ ከሃይማኖት አንፃር ምን አይነት ማህበረሰብ ነበር የሚኖርባት? እንደውም ጎንደርን በወቅቱ ከነበሩት የሃገሪቱ አካባቢዎች ለየት የሚያደርጋት ቤተ እስራኤሎች፣ ባህላዊ እምነት ተከታዮች፣ ሙስሊሞች፣ የውጭ ዝርያ ያላቸው ቱርኮች ሁሉም አንድ ላይ እንደልባቸው ተስማምተው የሚኖሩባት መሆኑ ነበር፡፡ በተለያዩ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎችም ይኖሩባት ነበር፡፡ አናፂዎች፣ ግንበኞቹ፣ ሸማ ሰሪዎች፣ የብረታ ብረትና የወርቅ ስራ የሚሰሩ እንዲሁም ነጋዴዎች ሁሉ አንድ ላይ ይኖሩባት ነበር፡፡ በጊዜው ንግዱን በሚገባ ያውቁታል ተብሎ ስለሚታመን ነጋድራሶች ከሙስሊሞች ነበር የሚመረጡት፡፡
  አፄ ፋሲለደስ ቤተ-መንግስታቸውን ካሳነፁ በኋላ በዙሪያው ሰባት ቤተ ክርስቲያኖችን አሰርተዋል፡፡ በየጊዜው ነገስታቱ እየተተኩ 120 ዓመታት እጅግ የረቀቀ የህንፃ ግንባታ ጥበብን ሰርተው አልፈዋል፡፡ የጎንደር ስልጣኔ የመጨረሻዋ ንግስት የነበሩት እቴጌምንትዋብም የራሳቸውን ቤተ-መንግስትና ቤተክርስቲያን  አሳንፀዋል ቁስቋም ትባላለች፡፡
አፄ ፋሲል ለምን 7 ቤተ-ክርስቲያናትን በዙሪያቸው አሰሩ?      
1
 አዘዞ /ሃይማኖት
2
 ፊት አቦ
3
 ፊት ሚካኤል
4
 አደባባይ ኢየሱስ
5
 ግምጃ ቤት ማርያም
6
 እልፍኝ ጊዮርጊስ
7
 //መድኃኔዓለም
       በወቅቱ እንደሚታወቀው ነገስታቱ በእምነታቸው ጠንካሮች ነበሩ፡፡ የጊዮርጊስ ታቦት ዘማች ታቦት ነው፤ ተዋጊ ነው፡፡ በአድዋ ጦርነት ጊዜም ቢሆን አፄ ምኒልክ ይዘው ዘምተዋል። የድንግል ማርያም ደግሞ ከንግስቲቱ ማረፊያ ቤት አጠገብ እንድትተከል ተደርጓል፡፡ ከትውፊቱ ከተቀበልነው ታሪክ እንደምንረዳው፣ አፄ ፋሲል ቤተ መንግስታቸውን ሲገነቡ አውሬ ሲያስቸግራቸው ባህታውያን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስን ታቦትን ትከል ብለው ሲመክሯቸው ያንን አደረጉ፡፡ መብረቅ ሲያስቸግራቸው የቅዱስ ሚካኤልን ታቦት፣ በሽታ ሲያስቸግራቸው የዓለም መድኀኒት የሆነውን የመድኀኒዓለም ታቦት እንዲተክሉ ተመከሩ፡፡ በዚህ ሂደት ነው ደብራቱን በዙሪያቸው የተከሉ ተብሎ ይነገራል፡፡ በሌላ በኩል በወቅቱ ካቶሊኮች ተባረው ፋሲል ይንገስ ሃይማኖት ይመለስ ተብሎ ሲታወጅ፣ አፄ ለሃይማኖታቸው ያላቸውን ፅናት ለማሳየ በርካታ ቤተ-ክርስቲያናትን እንደተከሉ ይታመናል፡፡
በዚያን ጊዜ የቤተ-መንግስቱ የአኗኗር ስርአት ምን ይመስል ነበር?
በአጠቃላይ የቤተ መንግስቱ ቅጥር ግቢ 70 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ነው ያረፈው፡፡ 12 በሮችም አሉት፡፡ ወደ ቅፅሩ የሚገባው እንደየደረጃውና ማዕረጉ በሚፈቅድለት በር ብቻ ነው፡፡ ራስች በር - ራሶች ብቻ የሚገቡበት ነው፣ የንጉሱ በር (ጃንተከል በር) ንጉሱ ብቻ የሚገቡበት ነው፡፡ ግምጃ ቤት በር የሚባል አለ -የግምጃ ቤት አስተናባሪዎች የሚገቡበት ነው፡፡ ቀጭን አሸዋ በር የሚባል አለ ይህ የግንባታ እቃዎች የሚገቡበት በር ብቻ ነው፡፡ እርግብ በር የሚባለው ደግሞ የደናግላን እና የመነኮሳት በር ነው፡፡ እንቢልታ ነፊዎች ብቻ የሚገቡበት ደግሞ እንቢልታ በር ይባላል፡፡ በሃዘን ጊዜ ሃዘንተኞች የሚገቡበት በር ተዝካሮ በር ይባላል፡፡ ተዝካሮ በር ፊት ከቤተመንግስቱ በስተደቡብ ባለው አነስተኛ ሜዳ ላይ አስከሬን ተቀምጦ ይለቀሳል፡፡ በጥንቱ የጎንደር ባህል ቦታው ሰዎች ሲሞቱ አስከሬናቸው ተቀምጦ ረዘም ላለ ሰአት ለቅሶና የሽኝት ስነ ስርዓት የሚከወንበት ነው፡፡ ባልደራስ በር የሚባለው ደግሞ ፈረሰኞችና የፈረሰኛ አዛዥ በር ነው፡፡ የንጉሱ ፕሮቶኮሎች የሚገቡበት በር ደግሞ ኳሊ በር ይባላል፡፡ በዚህ በኩል ባለጉዳዮችም ሆኑ የንጉሱ የቅርብ አጋዞች ይስተናገዱ ነበር፡፡
ንጉሡ በወቅቱ የከተማውን ህዝብ ግብር ያበሉ ነበር?
እንግዲህ በኢትዮጵያ ታሪክ ንጉሱ ግብር ካላበላ ምኑን ንጉስ ሆነው ይባል ነበር፡፡ ግብር ማስገበርም አለበት፡፡ ግብር በወርቅ፣ በብር፣ በከብት፣ በአሞሌ፣ በጥይት በመሳሰሉት መልክ ከነዋሪው ይሰበሰባል። ንጉሱ ደግሞ በምትኩ ለታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ግብር ሰብስቦ በየጊዜው ያበላል፡፡ ራሶችና መኳንንቶችም በየአውራጃቸው ላለ ህዝብ ግብር ማብላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ግብር ሲበላ ሰው እንደማዕረጉ ነው የሚቀመጠው፡፡ መጀመሪያ ንጉሱ ይቀመጣሉ፤ ከዚያ ንግስቲቷ ይቀጥላሉ፣ እጨጌውና የአክሱም ንቡረ ዕድ ይከተላሉ፡፡ እንዲህ እንዲያ እያለ መኳንንቱ በየደረጃቸው ይቀመጣሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ ከፋሲካ በኋላ ነው ግብር የሚበላው፤ በበአላትም እንደአስፈላጊነቱ ንጉሱ ደግሶ ህዝቡን ያበላል፡
ዳኝነት እና ፍርድስ እንዴት ነበር የሚከናወነው?
ዳኝነት እሚሰጠው እምነትን መሰረት በማድረግ ነበር፡፡ የእምነት ወይም ከፍተኛ ሃገራዊ ጉዳይ ከሆነና በመኳንንቱ መወሰን የማይችል ከሆነም ዙፋን ችሎት ላይ ይቀርባል፡፡ በእምነት ጉዳይ ክርክር ስለመካሄዱ ሁሌም በምሳሌነት የሚጠቀሰው የአልፈንዞ ሜንዴዝ እና የእጨጌ ጊዮርጊስ ክርክር ነው፡፡ በወቅቱ አልፈንዞ ሜንዴስ ከእጨጌው የሚቀርብለትን መከራከሪያ መመለስ አቅቶት ነበርና አንድ ጥያቄ ጠየቃቸው። ስላሴዎች ሁል ጊዜ ፀጉራቸውን የማይላጩት ለምንድን ነው?” በማለት እሳቸውም አንተ ቅንድብህን ትላጨዋለህን?” ሲሉ ጥያቄውን በጥያቄ መለሱለት፡፡ ቀጥሎም የአብ ፊቱ ወዴት ነው?” ሲል ጠየቀ፡፡ እሳቸውም ጧፍ አበሩና የዚህ መብራት ፊቱ ወዴት ነው?” አሉት፡፡ መልስ ሊሰጣቸው አልቻለም፡፡ በዚህም የእግዚአብሔር ፊት በሁሉም አቅጣጫ ነው ብለው ክርክሩን ረቱት ይባላል፡፡ ከፋሲል በኋላ አፄ (ፃድቁ) ዮሐንስ ነበሩ፡፡ እሳቸው የእንስሳትን መብት እስከማስጠበቅ የደረሱ ሰው ናቸው፡፡ ከደግነታቸው ብዛት ትልቅ ደውል በውጨ በኩል አስተክለው ነበር፡፡ ዳኝነት ጎደለብኝ ተበደልኩ የሚል ሰው መጥቶ ይደውላል፡፡ ከዚያም ይገባና ከንጉሱ ዘንድ ፍርድ አግኝቶ ይሄዳል፡፡ አንድ ጊዜ ምን ሆነ፡- ዝናብ እየዘነበ ነበር፡፡ ደውሉ ይደወላል፡፡ በዚህ ዝናብ ማን ፍርድ የጎደለበት ይሆን የመጣው ብለው እልፍኝ አስከልካያቸውን ይልኩታል፡፡ ኧረ ጃንሆይ አህያ ነው እንጂ ሰውስ የለም ይላቸዋል፡፡ አህያውን አስገባው አሉት፡፡ አህያው ሲታይ ጀርባው ተጋግጧል፡፡ ባለቤቱ ተፈልጎ ይቅረብ ተባለና መጣ፡፡ ለምን እንዲህ አደረክ፣ እድሜ ልኩን ያገለገለህን አህያህን ለምን ጣልከው?” ሲሉ ሰውየውን ገስጸው ቀጥተው ላኩት፡፡ አህያው ደግሞ በቤተ መንግስት ውስጥ ገብስና ባቄላ እየበላ እንዲኖርና ከቁስሉ እንዲያገግም ተደረገ፡፡ በዚያውም የተገጠበ አህያ ጭነት እንዳይጫን የሚለው አዋጅ ታወጀ፤ ጭኖ የተገኘም ይቀጣ ነበር፡፡ ያኔ ነው የእንስሳት መብት የታወጀው፡፡

ጎንደር 44 ታቦታት መገኛ ሲባል    ምን ማለት ነው?
ጎንደር ከመመስረቷ በፊት በአካባቢው አራት ደብሮች ነበሩ፡፡ አንደኛው አርባዕቱ እንስሣ ይባላል፡፡ በሌላ አቅጣጫ ቃአ ኢየሱስ የሚባል አለ፡፡ ጊዮርጊስ በሌላ አቅጣጫ አለ፤ አበራጊዮርጊስ የሚባልም አለ። ከዚያ በኋላ አፄ ፋሲል 7 ተከሉ፡፡ ፃድቁ ዮሐንስ 2 ተከሉ፣ አድያም ሰገድ ኢያሱ ደብረ ብርሃን ስላሴ ጨምሮ 2 ተከሉ፡፡ እንዲህ እንዲያ እያሉ ነገስታቱ በተፈራረቁ ቁጥር አዳዲስ ደብሮችን ሲተክሉ ኖሩ። በዚህ ሂደት በእነዚህ ነገስታት 30 ተተከሉ። 14 ያህሉ ደግሞ ቀድሞም የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ተደምረው ጎንደር 44 ታቦት መገኛ ሃገር ተባለች፡፡ ኋላ ላይ በደርቡሽ ጦርነት 4 ያህሉ ተቃጥለው ነበር፡፡ ሃገሬው የተቃጠሉትን እንደገና ሰርቷቸው ነበር፡፡ አሁን ሁለቱ እየተሰሩ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ሌሎች ደብሮች በብዛት የተተከሉ ቢሆንም የጥንቱን የጎንደር ስልጣኔ ለማስታወስ 44 ታቦታት የጎላ ቦታ አላቸው፡፡
ጎንደር የሚለው ስያሜስ ከየት የመጣ ነው?
ብዙ አፈታሪኮች አሉ፣ ነገር ግን ዋናው ማየት ያለብን የታሪክ ጥራዞችን ነው፡፡ የአፄ አምደፅዮን ዜና መዋዕል ላይ ጎንደር የሚለው ስም ሰፍሯል። ጎንደር ከመመስረቷ 300 ዓመት በፊት መሆኑ ነው፡፡ ወደ አፈታሪኩ ስንመለስ ቃሉ የማን እንደሆነ ባይታወቅም ጉንዳ ሃገር ወይም ትልቅ ሃገር ማለት ነው፡፡ አንዳንዶቹ ጓንግ እና ዳራ ከሚሉ ሁለት ቃላት የመጣ ሲሆን በአንገረብ እና ቃሃ ወንዝ መካከል ስላለች ነው ይህ ስም የተሰጣት ይላሉ፡፡ ግን የተጨበጠ ነገር የለውም፡፡

ነገስታቱ ይህን የቤተመንግስቱን ቦታ ከመያዛቸው በፊት ቦታው ላይ ምን ነበር?
እንደ አፈታሪክ እዚህ ቦታ ላይ (አሁን ቤተመንግስቱ ያለበት) ውሃ ነበር ይባላል፡፡ ውሃውን አድርቀው ቤተ መንግስታቸውን ሰሩ፤ አንዳንድ ታሪክ ደግሞ ቦታው የባላባቶች/የእርሻ ቦታ ነበር ይላሉ። ሌሎች አፈታሪኮች አፄ ፋሲል አደን ወጥተው አንዳንዶች ጎሽ ይላሉ ሌላው አንበሳ ይላል እያባረሩ መጥተው እዚህ ቦታ ሲደርሱ ተሰወረባቸው፤ ባህታዊ ተገልጦ ቤተ መንግስትህን የምትሰራበት ቦታ ይሄ ነው ብሎ ነገራቸው ይባላል፡፡ ከዚያ በፊት መላዕኩ ራጉኤል  የሚባል ቦታ ላይ ትነግሳለህ ብሎ በራዕይ ይነግራቸው እንደነበር ይነገራል፡፡  ሲላቸው ቦታውን ፍለጋ ጎዛራ፣ ጎጃም፣ ጎርጎራ ሄደው በመጨረሻ ጎንደር ፀንቶላቸዋል ነው የሚባለው። ነገር ግን በዚህ አካባቢ አድባራት በፊትም መኖራቸውን ስናይ ሰዎች ይኖሩበት እንደነበር ያመላክተናል፡፡ የኖህ መቃብር ነው የሚል ታሪክም ይነገራል? ሰዎች የራሳቸውን ታሪክ ይዘው ሊነሱ ይችላሉ። እኔም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይሄን ነገር ሰእየሰማሁ ነው፡፡ ይሁን እንጂ 1960ዎቹ የተፃፈ አንድ ታሪክ የሚያሳየው፤ ፋሲል ቤተመንግስቱን እንደ ኖህ መርከብ አድርጎ እንደሰራው ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ያለው ታሪክ የመጣው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው፤ ግን ሰፊና ጥልቀት ያለው ጥናት ይፈልጋል፡፡

   150 ዓመታቱ የጎንደር ስልጣኔ ከታዩ ዘመናዊ ነገሮች ጥቂቶቹን ቢጠቅሱልን
የቤተ መንግስቱ የህንፃ ጥበብ ዋናው ነው፡፡ አንዳንዶች የውጭ ሰዎች እጅ አለበት ይላሉ፤ ነገር ግን አሰራሩ በፊትም በአክሱም ዘመነ መንግስት የነበረ ነው፡፡ ህንዳውያንም ሆነ ፓርቹጋሎች ከመምጣታቸው በፊት እንደነበር ይናገራል፡፡ .. 1563-97 . የነገሱት አፄ ሰርፀድንግል ቤተ መንግስታቸው እንፈራዜ የምትባል ቦታ (ከጎንደር ወደ ባህርዳር ሲሄድ 60 ከሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ቦታ) ላይ የሚገኝ ቤተ መንግስት ላይ ይህ ቴክኖሎጂ  ተሰርቶበታል፡፡ ስለዚህ የውጭ ኃይሎች እጅ አለበት የተባለው አያሳምንም፡፡ ሌላው ግዙፍ የሆኑ የንግድ መስመሮች - እስከ አውሮፓ፣ ኤሽያ የሚዘልቁ ተፈጥረው ነበር፡፡ የቤተ መንግስቱን አኗኗር ካየን ደግሞ ዘመናዊ ነበር፡፡ ዛሬ ፋሽን የምንለው በዚያን ጊዜ ቀጭን ፈታዮች በሚባሉ ባለሙያዎች ለቤተ መንግስቱ ወይዛዝርት በየአይነቱ አልባሳት እየተሰሩ ያንን ፋሽን ይከተሉ ነበር፡፡ ዛሬ ስቲም የምንለው ያኔ ወሸባ ይባል ነበር፡፡ የፀጉር፣ የንቅሳት አይነት እንደፋሽን ይታይ ነበር፡፡ ዛሬ ዶሮ አስራ ሁለት ብልት አላት እንላለን። መለኪያ የወጣው በወ/ ምንትዋብ ጊዜ ነው። የዓሣ አሰራርና የተለያዩ የምግብ አሰራሮች ያኔ የመጡ ናቸው፡፡ ይህ ስርአት እንግዲህ ወደ ከተማው ተስፋፍቷል፡፡ እኛ ዛሬ የተጣራ ውሃ እያልን የታሸገ ውሃ እንጠጣለን፡፡ ይሄ በዚያን ጊዜም ይደረግ ነበር። የፈረስ ማቆሚያ (ፓርኪንግ) አገልግሎት ይሰጥ ነበር፡፡ ዛሬ የመኪና ፓርኪንግ እንደምንለው በአፄ በከፋ ዘመን ባለ ዘጠኝ በር ዘመናዊ የፈረስ ማቆሚያ /ፓርኪንግ/ ተሰርቶ ነበር፡፡ እንግዶች ፈረሶቻቸውን እዚያ ነበር የሚያቆሙት፡፡
5 ዓመት የጣሊያን ወረራ ቤተ መንግስቱ ለጣሊያን ገዢዎች መቀመጫነት አገልግሏል ይባላል?
   
      በሚገባ አገልግሏል፡፡ እንዲያውም ጣሊያን ከተማዋን ለሁለት ከፍሎ ነበር የሚያስተዳድረው። ከጃን ተከል በታች ያለው የሃገሬው ወይም የሃበሻ መንደር ነበር፡፡ አሁን ፒያሳ የምንለው ደግሞ የጣሊያኖች ነበር፡፡ ያኔ ሃበሾች ወደ ነጮች መንደር መዝለቅ አይፈቀድላቸውም፡፡ በቤተ መንግስቱ ውስጥም ለግብር በሚቀመጡበት ወቅት ነጮቹ በተመረጠ ቦታ ሃገሬው በሌላ ቦታ ሳይቀላቀሉ እንዲቀመጡ ይደረጋል፡፡ ምግብ ሲቀርብም ነጮቹ በስርአቱ ይመገባሉ፡፡ ሃበሾቹ ተሻምተው እንዲመገቡ ይደረግ ነበር፡፡ ጣሊያን ቤተ መንግስታቱ በጥቁሮች መሰራታቸውን አምኖ ላለመቀበል የፖርቹጋል ግንቦች ይላቸው ነበር፡፡ የከተማዋን ስያሜዎችም በብዛት ቀይሮ ነበር፡፡
ጃንተከል ዋርካ ዝነኛ ነው፤ ስለሱ ታሪክ ይንገሩን
ጃንተከል እንግዲህ አፄ ፋሲል ተከሉት ተብ ይታመናል፡፡ ለዚያም ነው ጃንሆይ የተከሉት ለማለት ጃን ተከል የተባለው፡፡ በወቅቱ የሃገር ሽማግሌዎች በስሩ ተቀምጠው ይወያዩ ነበር፡፡ ስቅላትን የመሳሰሉ ፍርዶችም ይፈፀሙበት እንደነበር በስፋት ይነገራል።

ጥንታዊ የጎንደር ሰፈር ስሞች

ጥንታዊ የጎንደር ሰፈሮች ስሞች  1. *ጥንታዊ ናቸው የሚባሉ እና ተመዝግበው የሚታወቁ 1.1. አደናግር ፡- ይህ ስም ከፋሲል ግንብ 12 በሮች ውስጥ አንደኛው የሚጠራበት ነው፡፡ በሩ በምስራቁ የግቢው ገጽ አዛዥ ጥቁሬ እና...